በልደታ ክፍለ ከተማ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ዝርዝር አገልግሎቶች
- 1. በተለያዩ አማራጮች የመኖሪያ ቤቶችን የማልማት አገልግሎት መስጠት፣
- በተለያየ የቤት ልማት ፕሮግራም የቤት ፈላጊዎች ምዝገባ አገልግሎት፣
- የጋራ ህንፃ መኖሪያ ቤት ህ/ሥ/ማ/አባላት ምዝገባ አገልግሎት፣
- ከመንግስት ጋር በአጋርነት በቤት ልማቱ ዘርፍ የሚሰሩ ባለሃብቶችን የመመዝገብና የመመልመል አገልግሎት፣
- የቤት አልሚዎች የሚያቀርቡትን ፕሮፖዛሎች በመገምገምና ውል የማዋዋል አገልግሎት፣
- የለማ መሬት በተለያዩ ፕሮግራም በአማራጭ የተደራጁ ማህበራት እና የቤት አልሚ ባለሀብቶች የማስረከብ አገልግሎት፣
- ለቤት ልማት ፕሮግራም የተገኘ የፋይናንስ ብድር የማስመለስ አገልግሎት፣
- ከጥቃቅን አነስተኛ ቢሮ የሚላኩ ኢንተርፕራይዞችን ወደ ስራ የማሰማራት አገልግሎት፣
- የቤት ልማት ጥናቶችን የማጥናት እና የመኖሪያ ቤት አይነቶችን በጥናት በመለየት፣ መደብና ደረጃ የማውጣት አገልግሎት፣
- ከቤት አልሚዎች እና ከነዋሪዎች የሚቀርቡ ቅሬታና አቤቱታዎችን በመቀበል ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣
- 2. የመንግስት ቤቶችን ለዜጎች በፍትሃዊነት ማስተላለፍ አገልግሎት፣
- በኪራይ የጋራ መኖሪያ ቤት የተመደበላቸዉን አካላት ዉል የማዋዋል አገልግሎት፣
- በልማት፣ በተፈጥሮ እና በሰዉ ሰራሽ አደጋ ምክንያት ለሚነሱ ተነሺዎች ምትክ ቤት የመመደብ አገልግሎት፣
- የሚቀርብ የቤት ቅይይር ጥያቄን በመቀበል ከመመሪያ አንፃር በማጣራት ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣
- በተላለፉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ ከፍርድ ቤት የሚመጡ የማስረጃ ጥያቄዎችን ተቀብሎ ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣
- ከተላለፉ አምስት አመት በሞላቸዉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ አምስት አመት ስለመሙላቱ የሚቀርብ የማስረጃ ጥያቄን ተቀብሎ ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣
- በተላለፉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ የሚቀርቡ የዉሃና የመብራት አገልግሎቶችን ተቀብሎ ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣
- በተላለፉ ቤቶች የሚቀርቡ ቅሬታ፣ አቤቱታዎችና ክሶች በመቀበል ምላሽ የመስጠት አገልግሎት
- 3. የመንግስት ቤቶችን ማስተዳደር አገልግሎት፣
- በኪራይ የተሰጡ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የኪራይ ውል ማደስ አገልግሎት፣
- የአደራ እና የማካካሻ ጥያቄዎችን ተቀብሎ መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣
- የቤት እድሳትና ጥገና ጥያቄ ተቀብሎ የማስተናገድ አገልግሎት፣
- የባለጉዳዮችን አቤቱታ በመቀበል የጥያቄውን አግባብነት ከመመሪያ አንፃር በማጣራት ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣
- ከመንግስት ቤቶች ጋር ተያይዞ ከተለያዩ አካላት የሚቀርቡ ክሶችን በመቀበል መረጃዎችን በማጣራት ምላሽ የመስጠት አገልግ