Welcome to Lideta Subcity Housing Development and Administration Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       Baga gara Waajjira Misooma fi Bulchiinsa Mana Jireenyaa Kutaa Magaalaa Lidetaatti dhuftan!

የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

ከተማችን አዲስ አበባን ሁሉም የሚለማባትና ለኑሮ የተመቸች ሞዴል ከተማ ለማድረግ በሚደረገው ከተማ አቀፍ ጥረት መኖሪያ ቤት የግድ ብቻ ሳይሆን የነዋሪዎች ህይወት መሻሻል፣ የህልሞች እና እድሎች መሳካት ሁሉ መሰረት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤትም ይህንን ቁልፍ የሆነ ሰው ልጆች ፍላጎትና የልማት መሰረት በክ/ከተማ ደረጃ ለመመለስ ተልዕኮ ተሰጥቶት እየሰራ ያለ ተቋም ነው፡፡ በክ/ከተማዋ ያለዉን ከፍተኛ የሆነ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለማሟላት ጥራት ያለውና ወጪ ቆጣቢ ቤት በማስገንባት፣ በፍትሐዊነት እንዲተላለፍ በማድረግ፤ ቀልጣፋና ውጤታማ የቤት አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋትና በመተግበር የክ/ከተማዋ ነዋሪዎችን ተጠቃሚነትን ማሳደግና በዚህም ህይወታቸው እንዲሻሻል፣ ህልማቸውን እንዲያሳኩና እድሎችን እንዲጠቀሙ የተልዕኳችን እምብርት አድርገን እየሰራን ነው፡፡

ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ የመጣውን የመኖርያ ቤት ችግር በዘላቂነት ለመፍታትም የተለያዩ ስልቶችን ቀይሰን እየሰራን እንገኛለን፡፡ በቀጣይም ተቋማዊ ለውጥ በማድረግ አሰራሮችን በማዘመንና በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዮቻችንን ፍላጎት በተሻለ መልኩ ለመመለስ ዝግጁ መሆናችንን እንገልጸለን፡፡..... ተጨማሪ ያንብቡ

አቶ ገመቹ ጌታቸው , የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
image description

በጽ/ቤቱ የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች

በልደታ ክ/ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች:-

Photograph

አቶ አሸናፊ ከበደ;
የቤቶች አስተዳደርና ልማት ስራዎች አስተባባሪ

የጽ/ቤቱ አስተባባሪ የሚከተሉትን ተግባራት ያከናዉናል:-
  • የቤቶች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት አገልግሎቶች ከአድልዎ ነጻ በሆነ መልኩ በእኩልነትና በፍትሀዊነት ተደራሽ በማድረግ የተገልጋዮችን እርካታ ማሳደግ
  • ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ያለው የአሰራር ስርአት ለማስፈን፣
  • አገልግሎት አሰጣጡ በተጠናው ስታንዳድ መሰረት እንዲሰጥ ማድረግ

የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክ/ከተማ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለውጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡

በተጨማሪም በጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ግንዛቤ በመፍጠር በዚህም ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በመሆኑም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂት ለመፍታት በምናደርገው ጥረት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሱቡ ከጽ/ቤቱ ጎን እንዲቆሙ እናሳስባለን፡፡