image
image
image
image
image

በመኖሪያ ቤት የተፈጠረውን የመልካም አስተዳር ችግር በተመለከተ በቀጣይነት መፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ግለፀኝነት ለመፍጠር ያለመ መድረክ ተካሄደ።

መስከረም 14, 2018
"የነዋሪዎቻችንን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል አስተዳደሩ በቁርጠኝነት ይሰራል!" ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሄደ። መድረኩ በመኖሪያ ቤት የተፈጠረውን የመልካም አስተዳር ችግር በተመለከተ በቀጣይነት መፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ግለፀኝነት ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ተገልጿል። የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደገለጹት የከተማው ብሎም የክ/ከተማው አስተዳደር የከተማዋን ነዎሪዎች የቤት ተጠቃሚ ለማድረግ በሰው ተኮር ስራዎች በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀው በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል። ወ/ሮ ልዕልቲ አክለው እንደገለፁት የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ባለሀብቶችን በማስተባበር፤ እጅግ የተጎሳቀሉና ምቹ ያልሆኑ ቤቶችን በማደስ፤ በሎው ኮስት፣ በኮንደሚኒየም ቁጠባ አማራጭ፣ በማህበር ግንባታ፣ በመንግስትና የግሉ ዘርፍ ትብብር፣ በህገወጥ መንገድ የተያዙ የመንግስት ቤቶችን በማስለቀቅ የቤት ችግሩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ግንዛቤ አስጨብጠዋል። በክ/ከተማችን በኢኮኖሚ እንዲሁም በአቅም ማነስ መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ሳያሟሉ ለችግር የተጋለጡ በርካታ ነዋሪዎች በመዲናዋ መኖራቸውን ገልፀዉ አስተዳደሩ ሰው ተኮር የ90 ቀን ዕቅዶችን በማዘጋጀት ችግሮችን ለመፍታት ርብርብ እያደረገ መሆኑን ወ/ሮ ልዕልቲ ገልፀዋል። ወ/ሮ ልዕልቲ አክለው የነዋሪዎቻችን የቤት ጥያቄዎች ውዝፍ በመሆናቸው ሁሉንም ችግሮችን በአንድ ጊዜ መቅረፍ ባይቻልም ደረጃ በደረጃ እየቀረፍን የነዋሪዎቻችንን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል አስተዳደሩ በቁርጠኝነት እየሰራ ነው ብለዋል። አቶ ገመቹ ጌታቸው የክ/ከተማው ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ በበኩላቸው የከተማው ውስን ሀብት የሆነው ከመንግስት ቤቶች ባሻገር የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ ከሚያስችሉት አንዱ የሆነው የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ቆጣቢ ነዋሪዎች የከተማ አስተዳደሩ ያዘጋጀውን ይህን አማራጭ ተጠቅመው በማህበር በመደራጀት እና በመቆጠብ የቤት ባለቤት መሆን የሚችሉ መሆኑን ገልፀዋል። የልደታ ክ/ከተማ መልካም አስተዳደር ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ በላይነህ ሙሉጌታ በመድረኩ ላይ እንዳሉት ከመኖሪያ ቤት ጠያቂዎች ጋር የተደረገው የግንዛቤ መፍጠር ስራ በአጠቃላይ የቤት ማስተላለፍና አስተዳደር በተመለከተ የነበረውን የተዛባ አመለካከት የሚያስተካክል መድረክ መሆኑን ጠቁመዋል። በመጨረሻም የውይይት መድረኩ ከተሳታፊዎች አስተያየት ተሰጥቶበት በመግባባት ተጠናቋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች