image
image
image
image
image

በልደታ ክፍለ ከተማ ባሉት 10 ወረዳዎች ከተውጣጡ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የእንጠያየቅ መድረክ ተካሄደ።

ህዳር 22, 2018
በመድረኩ ሦስት ጽ/ቤት ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት፣ ንግድ ፣ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎትና በተነቡ ሀሳቦች ላይ የጽ/ቤት ሀላፊዎች ምላሽ ሰጥተዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገመቹ ጌታቸው እንደተናገሩት በአንድ መአከል የአገልግሎትን አሰጣጡን የተሻለና የተቀላጠፈ ለማድረግ የተገልጋዩን ርካታ ያማከለ በቴክኖሎጂና በሰው ኃይልና ስምሪት ፈጣንና ቀልጣፋ በመረጃ የታገዘ አገልግሎት ለመስጠት በቁርጠኝነት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ንግድ ጽ/ቤት ወ/ሮ ተስፋነሽ ጋሻው በመድረኩ በተጠየቀው ጥያቄዎች ላይ በሰጡ ሀሳብ እንደገለፁት በቅዳሜና እሁድ አምራችና ሸማቾችን በቀጥታ በማገናኘት ጤናማ ግብይት እንዲኖር በማስቻል ገበያን የማረጋጋት ስራ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል። መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድ በመደበኛ የንግድ ስርዓት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳርፍ በመሆኑ ወደ ህጋዊ ስርዓት ማምጣት አስፈላጊ እንደሆነ አንስተው መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድ ስራ የሚመራበትን ስርዓት በመዘርጋት የተሰራው ስራ ውጤታማ መሆኑን ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ መቅደስ ያደታ ዘመናዊ የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ስርዓትን ተግባራዊ አድርጎ በመስራት የተማከለ የመረጃ አሰባሰብና አስተዳደር ስርዓት መዝርጋት እንደሚገባ ቀልጣፋ የሆነ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል። ጽ/ቤቱ የሲቪልና የነዋሪዎችን ምዝገባ ውጤታማነት በማረጋገጥ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ልማትን በማቀድና የዜጎችን አገልግሎት ለማሳለጥ ወሳኝ መሆኑን በመድረኩ ወ/ሮ መቅደስ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች