image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት የተገልጋዩን እንግልት ለመቀነስ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

ጥቅምት 16, 2018
የክፍለ ከተማው ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ገመቹ ጌታቸው እንደገለፁት ፅ/ቤቱ በየአመቱ የመንግስት ቤቶች ውል የማደስ ስራ ከዚህ በፊት በየወረዳው ሲሰጥ መቆየቱን ገልፀው በ2018 በጀት ዓመት የወረዳ መዋቅር በመታጠፉ ምክንያት አገልግሎቱ በክፍለ ከተማው እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል። አቶ ገመቹ አክሎም ተገልጋዮች አገልግሎትን ፈልገው ሲመጡ ፦ ቴሌ ብር ተጠቃሚ መሆንና ክፍያን በዛ መፈፀም፣ የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ኮፒ፣ የ2017 ዓ.ም ውል፣ ኪራይ የከፈሉበት ደረሰኝ፣ ተወካይ ከሆኑ ህጋዊ ውክልና ኮፒ፣ ወራሽ ከሆኑ የፍርድ ቤት የወራሽነት ማስረጃ ይዘው መምጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል ። ፅ/ቤቱ የተገልጋዮች እንግልትና መመላለስ ለማስቀረት የሚያስችለውን ፕሮግራም ያወጣ ሲሆን በዚህ መሰረትም፦ ከጥቅምት 17_23/2018 ዓ.ም ሰኞ ወረዳ 5=30 ቀበሌ ማክሰኞ ወረዳ 3= 26 ቀበሌ ዕሮብ ወረዳ 4=10 ቀበሌ ,ወረዳ 6=12 ቀበሌ,ወረዳ 8=11&12 ቀበሌ ሀሙስ ወረዳ 1=01ቀበሌ,ወረዳ 2=12 ቀበሌ,ወረዳ 10=17ቀበሌ አርብ ወረዳ 9=50ቀበሌ, ወረዳ 7=32ቀበሌ ቅዳሜ ወረዳ 5=43ቀበሌ,ወረዳ 3=36ቀበሌ እሁድ(ጥዋት) ወረዳ 5=42ቀበሌ መሆኑን ተገንዝበው ሁሉም ነዋሪዎች አገልግሎቱን በተቀመጠው መርሀ ግብር ብቻ መስተናገድ እንደሚችሉ ገልፀዋል። ማሳሰቢያ! ፅ/ቤቱ ቀጣይ ያሉትን ፕሮግራሞችን እያሳወቁ እንደምሄዱ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች